የርቀት ትምህርት መምህራን ከሥራ እየተሰናበቱ ነው

– አራት ኮሌጆች ከ98 ሚሊዮን ብር በላይ ከስረዋል እየተባለ ነው

(በታምሩ ጽጌ)

መንግሥት የትምህርት ሥልጠና ጥራትና አግባብነትን ለማረጋገጥ በሚል፣ ማንኛውም የግል ከፍተኛ ተቋማት የሕግና የመምህርነት ትምህርት እንዳይሰጡ ያስተላለፈውን ክልከላ ተከትሎ፣ በርካታ የርቀት ትምህርት መምህራን ከሥራ እየተሰናበቱ መሆኑን ለሪፖርተር ገለጹ፡፡