በመጪው ዓመት ከጨርቃ ጨርቅ ዘርፍ 85 ሚሊዮን ዶላር ይጠበቃል
– ዘንድሮ 50 ሚሊዮን ዶላር ታቅዶ 21 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ነው የተገኘው
(በውድነህ ዘነበ)
በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ የተገኘው ገቢ ከዕቅድ በታች ቢሆንም፣ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በሚቀጥለው የበጀት ዓመት ተጨማሪ ምርት ያስገኛሉ ያላቸውን ሦስት የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካዎች ታሳቢ በማድረግ 85 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት አቅዷል፡፡