በደርባኑ ጉባዔ አሜሪካ መበጥበጧን እንድታቆም ተጠየቀች

ደቡብ አፍሪካ ሽር ጉድ እያለች በምታስተናግደው የደርባኑ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ፣ አሜሪካ ቀዝቃዛ ውኃ እየቸለሰችበት በማስቸገሯ አደብ እንድትገዛና የሚካሄዱ ድርድሮች ከውጤት እንዳይደርሱ መበጥበጧን ጋብ እንድታደርግ ተሟጋቾች አስጠንቅቀዋል፡፡