በአዲስ አበባ የሚካሄደው የግብረሰዶማዊያን ስብሰባ ቁጣ ቀስቅሷል

የኃይማኖት አባቶች ድፍረት ይጎላቸዋል ተባለ

ተቃውሟቸው የታይታና ግብዝነት የሞላበት ነው

Ethiopia Zare (አርብ ህዳር 22 ቀን 2004 ዓ.ም. December 2, 2011)፦ በኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ ነገ ቅዳሜ፡ ኖቬምበር 3 በአፍሪካ የግብረ ሰዶማዊያን ቡድን አሰባሳቢነት በጤና ጉዳዮች ላይ በጁፒተር ሆቴል የሚካሄደው ስብሰባ በዚህ ሳምንት በህብረተሰቡ ዘንድ መነጋገሪያ ከመሆኑም በላይ በተለይ የሀይማኖት አባቶች የወሰዱት አቋም ቀድሞም ቁርጠኝነት ያልነበረውና ወላዋይነት የሞላበት መሆኑ ተገለጸ።