ከሶርያ የሸሹ ኩርዶች ቱርክ ገቡ

ቱርክ በሺዎች የሚቆጠሩ እና ከሶርያ የሸሹ ኩርዶች ድንበሯን ተሻግረው እየገቡ መሆኑን አስታወቀች። ከአማፂው አይ ኤስ ቡድን የሸሹ 45 ሺ የሚጠጉ ሰዎች ከዓርብ ዕለት አንስተው የቱርክ -ሶርያን ድንበር አልፈዋል ሲሉ የቱርክ ምክትል ጠ/ሚኒስትር ኑማን ኩርቱልሙስ ለCNN ቱርክ የመገናኛ ብዙኃን ገልጸዋል።