እስካሁን ለአይካሳ ጉባዔ የሚመጡ ተሳታፊዎች አምስት ሺሕ ብቻ ናቸው

‹‹ግብረሰዶማውያንም በጉባዔው ላይ ይገኛሉ›› የአይካሳ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ይገረሙ አበበ

የፊታችን እሑድ ኅዳር 24 2004 ዓ.ም. ለሚጀመረው አሥራ ስድስተኛው ዓለም አቀፍ የኤችአይቪና አባላዘር በሽታዎች የአፍሪካ ጉባዔ (አይካሳ) ኢትዮጵያ አሥር ሺሕ የሚሆኑ እንግዶች ይመጣሉ ተብሎ ይጠበቅ የነበረ ቢሆንም፣ እስካሁን በጉባዔው ላይ እንደሚገኙ ያረጋገጡት አምስት ሺሕ ገደማ የሚሆኑ ተሳታፊዎች መሆናቸውን የአይካሳ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ይገረሙ አበበ ለሪፖርተር አስታወቁ፡፡