‹‹የአሜሪካ ዕርዳታ የፖለቲካ መሣሪያ መሆን የለበትም›› ዶክተር ኢዝኪኤል ኢማኑኤል

(በታደሰ ገብረ ማርያም)

አሜሪካ የምትሰጠው ዕርዳታ የኅብረተሰቡን ጤንነትና የአኗኗሩን ሁኔታ ለማሻሻል የሚውል እንጂ፣ ለአገር ውስጥ ፖለቲካ መጠቀሚያ ወይም ማራመጃ መሣሪያ ሊሆን እንደማይገባ ዶክተር ኢዝኪኤል ኢማኑኤል የኋይት ሐውስ የጤና ልዩ አማካሪ አስታወቁ፡፡