የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቃውሞና የመንግሥት መልስ

በኢትዮጵያ ህገ መንግሥት ሃይማኖትና የመንግሥት አስተዳደር የተለያዩ መሆናቸው ተደንግጓል። ያም ሆኖ ኢትዮ አሜሪካውያን ሙስሊሞች የኢትዮጵያ መንግሥት በእስልምና ሃይማኖት ጣልቃ እየገባ ነው በማለት በቅርቡ የተቃውሞ ሰልፍ እስከማካሄድ ደርሰዋል ። እነዚሁ ተቃዋሚዎች በአሜሪካን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ፊት ለፊት ያሰሙትን ተቃውሞ የኢትዮጵያ መንግሥት መሰረተ ቢስ ሲል አጣጥሏል ። ሁለቱን ወገኖች ያነጋገረው የዋሽንግተን ዲሲው ዘገቢያችን አበበ ፈለቀ ዝርዝ ዘገባ አለው። ያዳምጡ