ከኔትወርክ ፍተሻ ጋር በተያያዘ ቻይናዊው የዜድቲኢ ባለሙያ የኢትዮ ቴሌኮም ኢንጂነሩን በስለት ወጋው
ዜድቲኢ የተባለው የቻይና የቴሌኮም ኩባንያ ከአዲስ አበባ በስተደቡብ 600 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው በነገሌ ቦረና አካባቢ የተዘረጋው የቴሌኮም ኔትወርክ ጥራቱ ተቀባይነት እንደሌለው በመግለጽ የተሠራውን ሥራ ውድቅ ያደረገው የኢትዮ ቴሌኮም ኢንጂነር፣ ኔትወርኩን በዘረጋው የዜድቲኢ ቻይናዊ ባለሙያ በስለት ተወግቶ ጉዳት እንደደረሰበት፣ ለፕሮጀክቱ ቅርበት ያላቸውና ድርጊቱን ያዩ የዓይን እማኞች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡