በአርበኛው የኔሰው ገብሬ ላይ የተከፈተው የስም ማጥፋት ዘመቻ አረመኔው የወያኔ አገዛዝ ምን ያህል የዘቀጠ እንደሆነ የሚያመላክት ነው ተባለ
ዘረኛውና አምባገነኑ የወያኔ አገዛዝ በህዝብ ላይ እያደረሰ ያለው ግፍና በደል ልኩን አልፎ ከሚሸከመው አቅም በላይ እየሆነ በመምጣቱ ራሱን በቤንዚን አርከፍክፎ ህይወቱን የሰዋውን መምህር የኔሰው ገብሬን የህይወት መስዋዕትነት ለማድበስበስ ወያኔ ሆን ብሎ የፈጠረው ”አይምሮው ጤናማ አልነበረም” የሚለው ሃሰተኛ ማስተባቢያ አገዛዝ ያለበትን የወረደ የዝቅጠት ደረጃ በግልጽ የሚያመላክት ነው በማለት አስተያየት ሰጪዎች ተናገሩ። በዳውሮና አካባቢው የሚገኙና ስማቸው ፍጹም እንዳይገለጽ የጠየቁት ወጣቶች ለግንቦት ሰባት ዘጋቢ በስልክ እንደገለጹት፣ በአካባቢው ተወላጆች በተለይም በቅርበት በሚያውቁት ዘመድ ወዳጆቹና ጓደኞቹ ዘንድ አክብሮት የተቸረው የኔሰው ገብሬ ህይወቱን ለነጻነትና ለፍትህ ተቆርቋሪነት ከገበረ ቦኋላ ወያኔ በሚቆጣጠራቸው የተለያዩ የዜና ማሰራጫዎች አሳዛኝ የሆነ የስም ማጥፋት ዘመቻ የተከፈተበት መሆኑ እጂግ አስገራሚና አሳፋሪ ከመሆኑ አልፎ በርካታ የህብረተሰብ ክፍልን እንዳስቆጣ ገልጸው ይህ የወያኔ ድርጊት የበለጠ ለትግል እንደሚያነሳሳቸውና ጥያቄቸውም ምላሽ እስከሚያገኝ የየኔሰውን አርማ ይዘው አገዛዙን እንደሚታገሉት ገልጸዋል።
ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ እያካሄደ ያለው የስም ማጥፋት ዘመቻ ምናልባት የኔሰው ገብሬ ማን እንደሆነ በቅርበት የማያውቁትን ግር ሊያሰኝ ይችል ይሆናል ያሉ እኙህ ምንጭ ይሁን እንጂ እዚሁ አብረነው ተወልደን ላደግን፣ በቅርብ ለምናውቀው ተማሪዎቹና ጓደኞቹ ለሆነው የአገዛዙ ባለሥልጣኖች የፖለቲካ ጥቅም እስካገኙበት ድረስ ምን ያህል ሂሊናቸውን አውርደው ርካሽ የሆነ ፕሮፖጋንዳ መንዛት እንደሚችሉ እንድንታዘብ አድርጎናል ብለዋል። በመጨረሻም አስተያየት ሰጪዎቹ የኔሰው፣ በጣም አስተዋይ የነበረ፣ የሚያደርገውን ለይቶ የሚያውቅ የፍትህ መዛባት እጂግ የሚያበሳጨውና፣ ይህንንም በግልጽና ባደባባይ የሚጋፈጥ ሰው ነበር፤ የኮሌጅ ተማሪ በነበረበት ጊዜ በጣም ጎበዝና የኮሌጁ ተሸላሚ የሆነ፣ አዘውትሮ መጻህፍት የሚያነብና አዋቂም ሰው ነበር ካሉ በሁላ፣ ጭራሹኑ የየኔሰው እህት ወንድሜ እብድ ነበር አለች ተብሎ በዜና መገለጹ ለመግለጽ የሚከብድ አሳፋሪና የዘቀጠ ድርጊት ነው ብለዋል።
ይህ በዚህ እንዳለ ዶቺቬለ የአማርኛ ዜና አገልግሎት በስዊድን ሃገር ነዋሪ የሆኑትን አቶ ፍስሃ ተሰማ የተባሉ የዋካ አካባቢ ተወላጅን ያነጋገረ ሲሆን አቶ ፍስሃ መምህር የኔሰው ገብሬን፣ እህቱንና ቤተሰቦችንም በሚገባ እንደሚያውቁ ገልጸው፣ የመምህሩ መሞት ብቻ ሳይሆን በተለይም ከሞተ ቦኋላ የሚነዛው የፈጠራ ወሬ ይበልጥ እንዳሳዘናቸው፣ የኔሰው ከሞተ ቦኋላ ለፖለቲካ ፍጆታ ተብሎ የሚነዛው ወሬና ማብራሪያ እንደሆነ ገልጸዋል። አቶ ፍስሃ ቀጥለውም ከመሞቱ በፊት ህዝብን ቀስቅሰሃል፣ የወረዳውን ችግር ጥያቄ አቅርበሃል፣ በሚል ነበር ታስሮ የነበረው። ይህ ታስሮ የነበረ ሰው ከተፈታና ህይወቱም ካለፈ በሳምንቱ የአይምሮ በሽተኛ ነው መባሉ በጣም የሚያሳዝን ነው። የአይምሮ በሽተኛና እብድ ነበር በማለት ስም ማበላሸት በየኔሰው የተጀመረ አይደለም፣ ከአሁን ቀደም አንድ አቶ አበራ የሚባሉ የአካባቢው ነዋሪ የግብርና ባለሙያ እብድ ነህ የአይምሮ በሽተኛ ነህ ተብለው ከስራ ከተወገዱ ቦኋላ የህክምና ዶክተሮች ጤነኛ መሆናቸውን በማረጋገጣቸው ወደ ስራቸው እንዲመለሱ ተደርጉአል፣ በዚያ አካባቢ፣ እንዲህ አይነት ስም መስጠት አዲስ አይደለም፣ ለምን እንዲህ እንደሚደረግም ፈጽሞ አይገባኝም ብለዋል።
አቶ የእኔ ሰውን እብድ ነበር አሉ የተባሉት እህቱ ናቸው ነው የተባለው እንዴት ይመለከቱታል፣ በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ አቶ ፍስሃ ሲመልሱ የሰው ልጅ አእምሮ ነጻነት ካጣ ለወንጀል ተባባሪና መሳሪያ መሆኑ የሚገርም አይደለም። ዋናው ጥያቄ እኒዚህ ሰዎች የአይምሮ ነጻነት አላቸው ወይ የሚለው ነው? በአካባቢው ከፍተኛ የነጻነት እጦት አለ፣ እውነት የመናገር፣ ያሰቡትንና የሚያውቁትን መግለጽ እጂግ ጠቃሚና ጥሩ ነበር። ነገር ግን የአካባቢው ሰዎች ይህን ማድረግ አይቺሉም። አንድ እህት እንደ ኢትዮጵያዊ ባህላችን ወንድሟ ከሞተ ቦኋላ እብድ ነበር ብላ ለህዝብ የምትናገርበት ሁኔታ በፍጹም ሊሆን የማይችልና የማይዋጥልኝ ነው። ነገር ግን ለመኖር ብለው ያሉት ሊሆን ይቺላል። ምናልባት የሚገርመው የየኔሰው እህትም ሆነች ሌሎች ዘመዶች ወያኔ አድርጉ ያላቸውን ባያደርጉ ነበር፣ እናም እኔን የወያኔ ባለስልጣኖች እያደረጉ ያለውም ነገር ሆነ የየኔሰው ዘመዶች አሉ የተባለው ነገር አዲስ አይደለም አያስገርመኝም፣ ብለዋል።