ሐበሻ ሲሚንቶ ከቻይና ኩባንያ ጋር የ79 ሚሊዮን ዶላር የፕሮጀክት ውል ተፈራረመ

– በዓመት 1.4 ሚሊዮን ቶን ሲሚንቶ ለማምረት አቅዷል

(በኃያል አለማየሁ)

ሐበሻ ሲሚንቶ አ.ማ. በሲሚንቶ ፋብሪካ ተከላና በግንባታው ዘርፍ ከሚታወቀው ኖርዘርን ሄቪ ኢንዱስትሪ ከተባለው የቻይና ኩባንያ ጋር በትናንትናው ዕለት በሒልተን ሆቴል በተከናወነ ሥነ ሥርዓት ላይ የ79 ሚሊዮን ዶላር የፕሮጀክት ውል ተፈራረመ፡፡