ሲኖዶሱ የፓትርያርኩ ሐውልት እንዲፈርስ ወሰነ

(በየማነ ናግሽ)

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ትናንት በዋለው ዓመታዊ ስብሰባ፣ በቦሌ መድኃኔአለም ቤተክርስቲያን ቅጥር ጊቢ ተሰርቶ የነበረው የፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ ሐውልት እንዲፈርስ፣ ከኢትዮጵያ ሚሌኒየም ጊዜ ጀምሮ በየቤተክርስቲያኑ ቅጥር ግቢዎች የሚገኙና ምስላቸውን የያዙ ቢልቦርዶች እንዲነሱ መወሰኑን ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡