ሲኖዶሱ የአቡነ ጳውሎስ ሐውልት እንዲፈርስ ወሰነ
”አልተሳሳትኩም፣ ሐውልት ማሠራት በእኔ አልተጀመረም” አቡነ ጳውሎስ
”ሐውልት መሠራቱን አላውቅም፤ ሐውልቱ ሲገለጥ ነው ያየሁት” አቡነ ጳውሎስ
Ethiopia Zare (ማክሰኞ ጥቅምት 16 ቀን 2003 ዓ.ም. October 26, 2010)፦ አዲስ አበባ ጉባዔ ላይ የተቀመጠው ቅዱስ ሲኖዶስ ከብዙ የአባቶች ውትወታ በኋላ ስለ ሐውልታቸው ጉዳይ ዛሬ ምላሽ የሰጡት አባ ጳውሎስ፤ ሁለት የተጻረሩ ሃሳቦችን በማቅረብ መደናገር እንዲፈጠር ቢያደርጉም፤ ሲኖዶሱ ሐውልታቸው እንዲፈርስና ፖስተሮቹም ከተሰቀሉበት እንዲነሱ ወሰነ።