በዋካ በርካታ ሰዎች እየታሰሩ ነው፤ ወያኔ ለሚያካሂደው የአገር ሃብት ዘረፋ በመሳሪያነት እያገለገሉ ያሉ የአካባቢው ባለስልጣናት በእጅጉ መደናገጣቸው ተነግሯል

የዋካ ነዋሪዎች እንደሚሉት መምህር የኔሰው ገብሬ እራሱን በእሳት አቃጥሎ ከገደለ በሁዋላ፣ በከተማው ውስጥ አመጽ ሊያስነሱ ይችላሉ የተባሉ ከ80 ያላነሱ ሰዎች ባለፉት ሁለት ቀናት መታሰራቸውን ኢሳት በትናትናው ዜና ዘገባው ገልጾአል።

እንደ ኢሳት ዘገባ እስካሁን ድረስ በተጫ ከተማ ብቻ ተወስኖ የነበረው እስር ወደ ገጠር መውረዱን የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ የአካባቢው ባለስልጣናት ህዝቡን ለማሸበር መሳሪያቸውን ታጥቀው በከተማው እየተዘዋወሩ እንደሚገኙና ለራሳቸውም በከፍተኛ ደረጃ እንደተረበሹ ታውቆአል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በፖለቲካ ጉዳይ ጣልቃ ገብተው ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨት ይሰራሉ ተብለው ከስራ እንዲታደጉ የተደረጉት የኦርቶዶክስ ቤቴክርስቲያን ሃላፊ የሆኑት በኩረ ትጉሀን ይልማ መኮንን የቀረበባቸውን ክስ ማስተባበላቸው ተዘግቦአል።

በኩረ ትጉሀን ይልማ እርሳቸው እንደማንኛው የአካባቢው ነዋሪ በግል የመብት እና የልማት ጥያቄዎችን ከማንሳትና ቤተክርስቲያኑዋ እንዳትዳከምና እንዳትደፈር ከማከላከል ውጭ በፖለቲካ ጉዳይ ጣልቃ አልመግባታቸውን ለኢሳት ተናግረዋል።

የቤተክርስቲያንቷን ሃላፊ ከስራ ያገዱዋቸው የዞኑ ሀገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ የሆኑት መምህር ወንዶሰን ክፍሌ ግን በኩረ ትጉሀን ይልማ ከስራ የታገዱት በፖለቲካ ጉዳይ ጣልቃ በመግባታቸው እንደሆነ እራሳቸው ለኢሳት በሰጡት ቃል እንዳረጋገጡ ለማወቅ ተችሎአል።

በዋካ ዞን በዳውሮ ቶርጫ የተነሳው ውዝግብና የመምህር የኔሰው ገብሬ ሞት በኢትዮጵያ ውስጥ የመነጋገሪያ አጀንዳ እየሆነ በመጣበት በአሁኑ ሰዓት በዘረኛው ወያኔ ሥር የሚተዳደሩ የሚዲያ ተቋማት ኢፍትሃዊነትን ተቃውሞ ህይወቱን በ እሳት ያጋየውን አርበኛ መስዋዕትነት ለማጣጣል መምህሩ የአይምሮ በሽተኛ የነበረ ነው ሲል ማስተባበሉ ተዘግቦአል።

ከወያኔ ልሳኖች አንዱ የሆነው ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል በትናትናው ዕለት በባለሥልጣናቱ የተፈቀነባበረ የሃሰት ህክምና ማስረጃ በማያያዝ በድህረ ገጹ ላይ ባወጣው ሪፖርት ሟቹ መምህር የኔሰው ገብሬ ህይወቱን ያጠፋው የአ እምሮ በሽተና ስለሆነ ነው ብሎአል። ለዚህም የሃሰት ማስተባቢያው በአካባቢው ነዋሪ የሆኑ ሰዎችን እንዳነጋገረና ገልጾአል። በተጨማሪም የቶርጫ ወረዳ ሆስፒታል ዋና ስራአስኪያጅ ነው የተባለ ግለሰብ ምስክርነት ለንባብ አብቅቶአል። ዋልታ ኢንፎርመሽን መምህር የኔሰው በኢሳት ቃጠሎ ሆስፒታል በገባበት ወቅት ህክምናውን የሰጡትን ዶክተር ከማናገር ይልቅ ለምን ከሙያው ጋር ምንም ግንኙነት ከሌለው የሆስፒታሉ ሥራአስኪያጅ ጋር ቃለመጠይቅ ለማድረግ እንደፈለገ የተሰወረ አይደለም።

በዋካ በተነሳው ህዝባዊ አመጽ እጅግ የተደናገጠውና የመምህር የኔሰው አር አያነት በሁሉም ስፍራ እንዳይሰራጭ ስጋት የገባው የወያኔ አገዛዝ የዳውሮ ዞን አስተዳዳሪ አድርጎ የመደበውን እስራኤል ኦታራ የተባለ ግለሰብ ኢንተርቪው በማድረግ እውነተኛውን ዜና ለህዝብ ጆሮ እያደረሱ ያሉትን ኢሳትና የአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው ክፍል እንዲያወግዝና ከማድረግ አልፈው “ የኢትዮጵያን ህዝብ ለማተራመስ ከያዙት አጀንዳ እንዲቆጠቡ”በማለት ማሳሰቢያ እንዲሰጥ እንዳደረጉት ተዘግቦአል።

የዳውሮ ዞን አስተዳዳሪ ተብዬው ይህ ግለሰብ “ኢትዮጵያ ውስጥ አመጽና ሽብርተኝነትን ለማስፋፋት በሚያደርጉት እንቅስቃሴ በአሸባሪነት የተፈረጁ ቡድኖች የተዛባና የሀሰት ዘገባዎችን በማሰራጨት በህዝቡ ላይ ውዥንብር ለመፍጠር የሚያደርጉት ጥረት ዋጋ የለውም እንዳለና በተለያዩ ጊዜያት የኢትዮጵያን ህዝብ ለአመጽ የሚቀሰቅስ ጥሪ ሲያቀርቡ ህዝቡ በበኩሉ ጆሮውንም ልቡንም ስለነፈጋቸው የሟች የኔሰውን አሟሟት ከቱኒዚያው ወጣት ጋር ለማመሳሰል ያደረጉት ጥረት ቀቢጸ ተስፋቸውን እውን ለማድረግ የተጠቀሙት ዘዴ መሆኑን ማንም መረዳት አያዳግተውም ብሎ መናገሩን ዋልታ ገልጾአል።

ከሁሉም የሚገርመው አብዛኛው የአገራችን ወጣትና ጎልማሳ አገሪቱ ውስጥ በተስፋፋው ኢፍትሃዊነትና ድህነት ተማሮ አገሩን ጥሎ እየተሰደደ ባለበት በአሁኑ ወቅት፤ በሃብት ዘረፋ የከበሩ የወያኔ መሪዎች በራሳቸው ድሎትና ምቾት አገር እየመዘኑ ስለልማትና እድገት፤ ፍትህና ብልጽግና በሚደሰኩሩት ባዶ ፖርፖጋንዳ እራሳቸውንና ጄሌዎቻቸውን አሳምነው አገራችን ውስጥ ህዝባዊ አመጽ የሚቀሰቅስ ችግር የለም ሲሉ መስተዋላቸው ነው። ለዚህም ይመስላል ወያኔ በቶርጫ የመደበው አስተዳዳሪ አገራችን ውስጥ እየተቀጣጠለ ያለውን ተቃውሞ ለማጣጣል ሲናገር “በመላው አለም የተከሰተውን የኢኮኖሚ አለመረጋጋትና በተለይ በአረቡ ሀገራት ለዘመናት ስር ሰዶ የቆየውን ንጉሳዊ ስርዓትና ኢ-ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ከሚቃወሙ ህዝቦች ጋር ኢትዮጵያን ማመሳሰል አላዋቂነትና ሀገሪቱም እንዲህ ያለውን የእርስ-በርስ ግጭት ከ20 አመታት በፊት እንዳለፈችው ያለመረዳት ውጤት ነው ያለው።

ዋልታ ዘገባውን ያጠናቀቀው “ ለርካሽ ፖለቲካ ጠቀሜታ ሲሉ እውነትነትን የሌለውን መረጃ በማሰራጨት በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የተረጋጋ ፖለቲካ ለማደፍረስ የሚፈልጉ በውጭ ያሉ ሚዲያዎች በተለይም ኢሳትና ቪኦኤ ከእንደዚህ አይነት ድርጊታቸው እንዲታቀቡ የዳውሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የሟች ቤተሰቦች አስጠንቅቀዋል በማለት ነው። ሆኖም ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማእከል በዋካ ከተማ የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ ለማስተባበል አልደፈረም።

ኢሳት የመንግስት ባለስልጣናት ሟቹ የአእምሮ በሽተኛ ነው ብላችሁ በሉ በማለት ነዋሪዎችን ሲያዋክቡ እንደነበር ቀደም ብሎ ዘግቦ እንደነበር አይዘነጋም።