የአቶ ግርማ ብሩ የዳላስ ጫራታ ከአገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን/ዳላስ
ስብሰባው ከመደረጉ አስቀድሞ ሕዝብ እንዲያውቀው አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን አንድ መልእክት አስተላልፈው ነበር። ቅዳሜ ኖቨምበር 12 ቀን 2011 በኢንተር ኮንትኔንታል (Intercontinental Hotel) ሆቴል የኦሕዴድ አባል የሆኑት የኢሕአዴግ አምባሳደር አቶ ግርማ ብሩ ስብሰባ አድርገው ነበር። ስብሰባው የእራት ምሽት በሚል የተጠራ ሲሆን። አንድም ተቃዋሚ ተብሎ የተጠረጠረን ሰው ላለማስገባት፤ በግል ደብዳቤ የተጠራ በመሆኑ፤ የዚህ አንባገነን መንግስት ተቃዋሚወች በግርማ ብሩ እራት ምሽት አልተገኙም። ይህ አድራጎት ሕወሐትም ሆነ ኢሕዴን (በበረከት ስምኦን የሚመራው ስሙን ብሔረ አማራ ዴሞክራሲ ምናምን) ብሎ የሚጠራው ቡድኖች የመንግስት ስልጣን ከመያዛቸው በፊት ያደርጉ እንደነበረው፤ ደጋፊን ብቻ ሰብስቦ መምከር አይነቱን ተግባር በዚህ ስብሰባ ፈጽመዋል።፡ግለሰቦች በደብዳቤ ተጠርተው ምልክት ያለውን ኦሪጅናል ደብዳቤ ይዘው እንዲገቡ ተደርጓል። መላ ቴክሳስንና ከአጎራባች እስቴቶች የመጡ የኢሕአዴግ/ሕወሐት ደጋፊወች ተሰብስበው አምሽተዋል። ይመጣል ያሉት የዳላስ ነዋሪ ኢትዮጵያዊም ሆነ፤ እናገኛለን ብለው ያሰቡት የፖለቲካ ጥቅም ግን እውሀ እንደበላው ለመረዳት ችለናል። የአማራ ልማት ማሕበር (አልማ) በሚል የተደራጁ የሕወሐት/ኢሓዴግ ደጋፊወች ያው አንድ ፍሬ ሆነው ምናልባት ቱባ ነጋዴ የሆኑና ምናልባትም በደጅ ጽናት ላይ ያሉ አንድ ሁለት ከመጨመር በቀር የተጠራው የሕዳሴ ቦንድ አንድ ገጣሚ እንዳሉት እዉሐ በላው በሚያሰኝ ሕዝብ ይህን ቧልት ላይቀላቀል ንቆ አልፎታል።
ቀኑ ከመድረሱ አስቀድሞ በአይጋ ፎረም (የሕወሐት/ኢሓዴግ አፈላማ) በሆነ ድህረ ገጽ ለማስታወቂያ ተለጥፎ በነበር ደብዳቤ አልማወች አዳራሹ ስለሞላ ከዚህ በኋላ ማስተናገድ ይሳነናል የምትል የጮሌ መልእክት እንደጻፉ የሚዘነጋ አይደለም። ቅዳሜ በስብሰባው ቀን ግን ከኦክላሆማ ስቴት፣ ከኦስተን ቴክሳስ፣ ከሂውስተን ቴክሳስ፤ ከሉዚያናና ከፎርትወርዝ የመጡ diehard ደጋፊወች ተጨምረው እራስ እግሩ ተሰብሳቢ 175 ብቻ እንደነበር ዜናው ደርሶናል። ይህን አስመልክቶ ከስብሰባው አስቀድሞ ባወጣነው መልእክት እንዳልነው፤ ጨቋኞችና አድር ብየወች የሕዝብን ግፍ ከጉዳይ አይቆጥሩም እንጅ የወጋ ቢረሳ የተወጋ አይረሳም እንደሚባለው። ይህ ዘረኛና ከፋፋይ መንግስት ሕዝብን በፕሮፓጋንዳ ለማውለቅ ሲከጅል አይገባም ያሉ ወገኖች የካድሬወችን ያውም የአማተር (amateur) ካድሬን ጥሪ አለመቀበሉ ያለነገር እንዳልሆነ ሊያውቁ ይገባል።
ከተሰበሰቡት ውስጥ ፕለጅ ያደረጉ እንደነበሩም ሰምተናል። ያም ቢሆን ትቂቶቹ ያገኙትን ወረታ መላሽ ለመሆንና እነሱ ቁጥሩ ከፍ ያለ ገንዘብ በመጥራት ሌላውን ለማስወጣት ሞክረው ነበር። መጦ ነበር ተብሎ ሶሊዳሪቲ ለማሳየት የሄደው አንዳንድ ግለሰብ ፊቱን አስመትቶ ምንም ሳይሰጥ መውጣቱንም ሰማን። በጠቅላላ ሕወሐት አገኛለሁ ብሎ ያሰበው የፖለቲካም ሆነ የህዳሴ መዋጮ አለመሳካቱን፤ የዳላስ ኢትዮጵያዊም ከቤተሰብ ጋር በየጊዜው የሚገናኝ ሰርቶ አዳሪና ወገኑን የሚረዳ በመሆኑ፤ የአቶ ግርማ ብሩም ሆነ የአልማ ቅስቀሳን ከቁብ ሳይቆጥረው ቀርቷል። ዛሬ በግፍ ወደ እስር በመወርወር ላይ ያሉ ንጹሐን ወገኖቻቸውን የሚረሱና ለመናኛ ፕሮፓጋንዳ የሚፈቱ አይደሉም። ለዚያም ሌት ከቀን ዙረው የቀሰቀሱትን ወዶ ገብ አማተር ካድሬወች ጀሮ ነስቷቸዋል። አማተር ካድሬ ስንል፤ ደመወዝ ተቆርጦላቸው ሳይሆን ከዛሬ ነገ ተቀባይነት እናገኛለን ያሉ በጣት የሚቆጠሩ ደጅጠኝ ግለሰቦች በመሆናቸው ነው።
አቶ ግርማ ብሩ የተከዜን ግድብም ሆነ የግልገል ጊቤን ግድቦች በመልካም ምሳሌነት ማቅረብ ባለመቻላቸው ደጋፊወቻቸው የተሰበሰቡበትን የእራት ምሽት ጀሮ ሊስቡ አልቻሉም። ለምሳሌ ከሱዳን በ20 ኪሎሜትር እርቀት ላይ የሚገነባው ያሉትን ታላቅ ፕሮጀክት፤ደህንነቱን አስመልክቶ እመኑን ከማለት ባለፈ የተጨበጠ መልስ አልንበራቸውም። ሕወሐት/ኢሕአዴግ የሰሜን አፍሪካ አብዮት በተነሳበትና ጨቋኝ መንግስታትን በናጠበት ሰአት የተዘየደ የሕዝብን ትኩረት የማስቀየር መለሳዊ መላ ነው የሚለውን አሁንም ቢሆን እንኳን ግርማ ብሩ የስርአቱ ፈጣሪወች አይመልሱም።
በተቃዋሚው በኩል የቀረቡ ግድቡን የማይቃወሙ መሆኑን ግን ግድቡ ያልታሰበበትና እለፍ ተቀደም የሚጠይቅ፤ የአፈርና የተፈጥሮ አየር ሁናቴን የማያዛባ መሆኑን አለማቀፍ እውቅና ባለው አካል ማስጸናትና ማቅረብን አይነት ቅድመ ሁኔታወች የሚጎድሉት መሆኑን። ከዚህ በፊት የተሰሩ ግድቦች እንዳስተማሩን የግልገል ጊቤ ለምሳሌ ሊያስከትል የሚችለው የአየር ጸባይ ቀውስ ፈጽሞ ያልታየ መሆኑ። ሊሰጠው የሚችለው የኢኮኖሚ ጥቅም ሊያስከትል ይችል ይሆናል ከተባለው በደቡባዊ የኦሞ ተፋሰስ ቀበሌወች የዝናብ መጥፋትና የድርቅ መከተል አንድ ችግር የሚሆን በመሆኑ የሚሉትን ሁሉ ሳይናሳዊ አጋጣሚወች በዚህ አሁን በመቀስቀስ ላይ ላለው ግድብ ያልጨመረ መሆኑ የሁላችንም አሳሳቢ ጉዳይ ነው። ሕወሐት አገር ሲቆጣጠር አያስፈልገኝም ያለው የአሰብ ወደብ በከፍተኛ ወጭ እገድባለሁ ከሚለው ግድብ የበለጠ አመታዊ ጥቅም የሚያስገኝ ከመሆኑ ባሻገር፤ ለአገሪቱ ደህንነትና እራስን የመጠበቅም እስትራቴጅያዊ ጥቅምን አሳልፎ የሰጠ ለመሆኑ መታወስ ይኖርበታል።በእርግጥ አባይ መገደብ አለበት። ሲገደብ በአገሪቱ ጠበብቶች ታምኖበትና ተጠንቶ ሊሆን ይገባዋል። ያም ሲሆን ከአደጋ ነጻ በሆነና፣ ሁሉም ዜጋ ከትውልድ ትውልድ እንደዘፈነለት፡ ለግድቡም በፍቅር እንዲዘፍንለት ተደርጎ መሆን ይኖርበታል። ብሎም የሁሉን ዜጎች ቅን ትብብር የሚፈልግ እንጅ። አስበንላችኋል ተብሎ በዱብዳ የሚወረወርባቸው አይደለም። ይህን ሀላፊነት ያለውን መከራከሪካ በመናኛ ጸረ ልማት አስመስሎ ለማቅረብ ሲሞክሩ አሁን ባይሆን ጊዜ ይታዘባቸዋል። የዳላሱ የስብሰባ ጥሪም የገጠመው ይኸው የዝምታ ተቃውሞ እንደሆነ ለመማር ከፈለጉ አሳይቷቸዋል። አቶ ግርማ ብሩ ብሩህ አእምሮ ካላቸው እራሳቸው እንዳሉት 30,000 ኢትዮጵያዊ በሚኖርበት ከተማ ከ50 ያልበለጡ መገኘታቸውና ያነን የስብሰባና የእራት ምሽት ከደቡባዊ ዩናይትድ እስቴትስ ግዛቶች በተሰባሰቡ ግን ቁጥራቸው 175 ከሆኑ ጋር ማሳለፋቸው የዚህ መንግስት ተአማኒነት ከራሱ አባላትና ትቂት ደጋፊወቹ ያልወጣ መሆኑን በውስጠ ልቦናቸው መቀበላቸው እንዳልቀረ እንገምታለን። ይህ ተግባር እርሳቸውን ጨምሮ ለዚህ መንግስት ላደሩ ግፈኛን ለሚደግፉ ሁሉ ትምህርት ሰጭ ነበር። በተለየም በአሁኑ ሰአት ነጻ ጋዜጦችን ዘግቶ ጋዜጤኞችን በግፍ በሐሰት ውንጀላ በሚያስርበት ሰአት። ወገን ተሰብስቦ ይህን ግፈኝነት እንዲቃወም እንጅ። አሳሪና አንገላቹን አገዛዝ እንዲደግፍ አይጠበቅም። ዳላስ ነዋሪ የሆነው ኢትዮጵያዊ በግርማ ብሩ ድካም አፊዞበታል። በ $50 ዶላር የእራት ምሽት ከፍለው የገቡት እነዚያ በእጣት የተቆጠሩት ቦንድ ሳይሆን የሁለት ዜግነት ፈቃድ በ $100 ይገዛልን ሰምተው ስለሆነ። ያሰቡት ሳይሳካ ቦንድ ያልገዛ ዜግነት አይሰጠውም ተብለው በመጡበት ተመልሰዋል። ምስጋና ለዳላስ ኢትዮጵያዊ የግፈኞች ካድሬወች አፈሩ። ደጅ ጠኞች በግላጭ አምባሳደሩን አገኙ። ትቂት ንብረት አለን የሚሉ ከሁለት ወይንም ሦስት ያልበለጡ ቦንድ ገዛን ብለው ተንደፋድፈዋል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ
ለግፈኞች የጋዳፊን ቀን ለማየት የጊዜ ጉዳይ ነው
አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን/ዳላስ
[email protected]