የፌዴራል ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ከተከሰሱበት የሙስና ወንጀል በነፃ ተሰናበቱ

(በታምሩ ጽጌ)

የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃቤ ሕግ በተጠረጠሩበት የ100 ሺሕ ብር የሙስና ወንጀል ክስ መስርቶባቸው የነበሩት የፌዴራል ፖሊስ ሕዝብ ግንኙነትና ጉዳዮች ኃላፊ ኮማንደር ደምሳሽ ኃይሉን፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት ጥቅምት 12 ቀን 2003 ዓ.ም. በነፃ አሰናበታቸው፡፡