የአዲስ አበባ አስተዳደር ከነዋሪው 600 ሚሊዮን ብር ይፈልጋል

– ገንዘቡን ለማሰባሰብ የምርጫው ‹‹ኔትወርክ›› ሥራ ይጀምራል

(በውድነህ ዘነበ)

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከሁለት ዓመት የሥልጣን ቆይታ በኋላ የቀድሞውን የከተማውን ጊዜያዊ አስተዳደር ዱካ በመከተል፣ ከነዋሪው ሕዝብ 600 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ሀብት በማሰባሰብ የልማት ሥራዎችን ማካሄድ የሚያስችለውን አዲስ ዕቅድ ይፋ አደረገ፡፡