የኃይል ፈረቃና ታሪፍ ጭማሪ ይጠበቃል

(በዳዊት ታዬ)

ባለፈው ማክሰኞ ጥቅምት 9 ቀን 2003 ዓ.ም. በፓርላማ የመንግሥትን አቋም ያስረዱት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ፣ አገሪቱ የገጠማት የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ከሥርጭት ኋላቀርነት የመነጨ መሆኑን አስረድተዋል፡፡