በሽብር ወንጀል የተከሰሱት 24 ተጠርጣሪዎች ክስ ሳይሰማ ቀረ

ከኤርትራ መንግሥት፣ ከኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) እና ከኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ጋር ጥምረት በመፍጠር፣ የግንቦት 7 ድርጅት አመራርና አባል በመሆን፣ ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለማፈራረስ ሲንቀሳቀሱ ተገኝተዋል በሚል 17 ገጽ ክስ የቀረበባቸውና በሽብር ወንጀል የተጠረጠሩ 24 ተከሳሾች ክስ በትናንትናው ዕለት ሳይሰማ ቀረ፡፡