የዘረኛው እና ፋሽስቱ መለስ ዜናዊ ባለቤት አዘብ መስፍን በጫት ንግድ በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ እንደምታገበስብስ ታወቀ
በወያኔ ቁንጪዎች አፈና ምክንያት ወደኢትዮጵያ የሚያደርገውን የሳተላይት ስርጭት ለጊዜው እንደተቋረጠበት የሚታወቀወ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴለቪዥን ኢሳት ፤ በውጪ አገር ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በኢንተርነት በሚያሰራጨው የስትሪሚንግ ቴለቪዥን አገልግሎት ባለፈው ቅዳሜ ባሰራጨው ዜና በግል ድርጅት ስም በጫት ንግድ ከተሰማሩት 7 ድርጅቶች አንዱ የወያኔው ቁንጮ መለስ ዜናዊ ሚስት መሆኗንና መንግሥት ከጫት ንግድ ማግኘት ከሚገባው ገንዘብ በአመት ከ200 እስከ 500 ሚሊዮን ብር የሚደርስ ገንዘብ መንግስት ካዝና ሳይገባ እንደሚመዘበር ከንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ያገኘውን መረጃ ዋቢ በማድረግ አጋልጦአል።
ከታማኝ ዜና ምንጮቹ ያገኘውን ይህንን መረጃ አጣቅሶ ለህዝብ ይፋ ያደረገው ኢሳት ፤ በአሁኑ ጊዜ በጫት ንግድ ስም ከፍተኛ የሆነ ትርፍ በማጋበስ ሥራ ላይ የተጠመዱት አንዱ የኦሮሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ( ኦህዴድ) ንብረት የሆነው በዲንሾ ኢንዶውመንት ፈንድ ስር የሚገኘው ቱምሳ የንግድ ድርጅት እንደሆነና ሌላው ደግሞ አዜብ መስፍን በባለቤትነት የሚትቆጣጠረው የሀርጌሳዋን ነጋዴ ሱራ ሙሀመድን በሽርክና የያዘው የንግድ ድርጅት መሆኑን ይፋ አድርጎአል; ;
ኢሳት ባገኘው መረጃ መሰረት 90 በመቶ የሚሆነውን የጫት ምርት ወደ ውጭ ገበያ የሚያቀርበው የአዜብና የሱራ ድርጅት ሲሆን፣ ከ1997 እስከ 2001 ድረስ 113 ሺ 960 ቶን ጫት ወደ ጎረቤት አገሮች በመላክ ፣ ከ512 ሚሊዮን 233 ሺ የአሜሪካን ዶላር በላይ ትርፍ ተገኝቶበታል ።
ሌሎች 5 ድርጅቶች 10 በመቶ የሚሆነውን ምርት ብቻ መላካቸው የታወቀ ሲሆን ፣ የዘረኛው እና ፋሽስቱ መለስ ባለቤት ድርጅት ግን ለማንም ያልተፈቀደውን የካርጎ አውሮፕላን በመከራየት በቀን እስከ አራት ጊዜ በሚደርስ በረራ በጅቡቲ፣ በሀርጌሳና በሌሎችም ቦታዎች ጫት እንደሚያመላልስ ታውቋል ብሎአል ኢሳት ።
እንደ ኢሳት መረጃ ቀደም ብሎ የሀርጌሳን ገበያ በቱምሳ ንግድ ድርጅት ስር የሚገኘው በልበላ የተባለው የጫት ላኪ ክፍል ይቆጣጠረው እንደነበረና መለስ በሚስቱ አዜብ በኩል ወደ ንግዱ ገበያ ከመጣ ቦኋላ በኪሳራ እንዲወጣ እንደተደረገ እና የአዜብና የሶራ ድርጅት የምስራቅ ሀረርጌ ገበሬዎችን ማሳ እንዳለ በመግዛት ገበሬዎቹ ምርታቸውን ለሌላ ነጋዴ እንዳይሸጡ በማስደረግ ዲንሾና ሌሎች ድርጅቶች ጭምር ከገበያ እንዲወጡ እየተደረገ ነው ተብሎአል።
ቀደም ብሎ የኦሮሚያ ክልል በክልሉ የተለያዩ ቦታዎች ኬላዎችን በማስቀመጥ በኪሎ 6 ብር ቀረጥ ይቀበል እንደነበር የኢሳት መረጃ ምንጮች ሲናገሩ ፤ የጫት ኤክስፖርትን ለማበረታት በሚል ሰበብ ኬላዎች እንዲነሱ በመደረጋቸው የኮታ ስርአቱ እንዲቀርና ቀረጥ መሰብሰቡም እንዲቋረጥ እንደተደረገ ለማወቅ ተችሎአል።
በዚህ አሰራር ቅር የተሰኘው የኦሮሚያ ክልል በያመቱ ከቀረጥ የሚያገኘው እስከ 500 ሚሊዮን የሚደርስ ብር በኬላው መነሳት ምክንያት በመቋረጡና የክልሉ ገቢ የመሰብሰብ ስልጣን ለፈደራል መንግስት አሳልፎ በመሰጠቱ ለፋሽስቱ መለስ ዜናዊ አቤቱታ አቅርቦ እንደነበር ነገር ግን ዘረኛው መለስ ” እርምጃው የተወሰደው ኤክስፖርትን ለማበረታት ታስቦ ነው የሚል መልስ ከመስጠት አልፎ ተቃውሞ ባቀረቡት የኦሮሚያ ባለስልጣናት ላይ ቅሬታ ማሳደሩን ኢሳት ያገኘው መረጃ እንደሚጠቁም ተዘግቦአል።
ከጫት የሚገኘው የውጭ ምንዛሬ ወደ መንግስት ካዝና እንደማይገባ መረጃ የደረሰው የብሄራዊ ባንክ፣ ጉዳዩን የሚያጣራ አንድ ኮሚቴ የሰየመ ሲሆን፣ ኮሚቴው የኬላው መነሳት አግባብ አለመሆኑን በመጥቀስ ለመለስ ዜናዊ ደብዳቤ ቢጽፍም መልስ ሳይሰጡበት አስከዛረ እንደተቀመጠ ኢሳት አያይዞ ዘግቦአል።
የአንድ ኪሎ ጫት ዋጋ በጂቡቲ ከ7 እስከ 8 ዶላርና በሀርጌሳ 10 ዶላር መሆኑን የጠቀሱት ምንጮች ከ1997 እስከ 2001 ድረስ ከ100 ሺ ቶን በላይ ጫት ለጎረቤት አገሮች ተልኳልም ብሎአል።