በብራስልስ የሚገኘው የዘረኛው ወያኔ ኤምባሲ ወደ አንድ መቶ ለሚጠጉ ሆድ አደሮች ግብር ማብላቱ ታወቀ

በአውሮጳ ህብረት የወያኔ አምባሳደር የሆነው ብርሃኔ ገብረ ክርስቶስ ባለፈው ቅዳሜ ጥቅምት 6 ቀን 2003 አም የኢትዮጵያን አድስ አመት ለማክበር በሚል ሽፋን በቤልጅዬም እና አካባቢዋ የሚኖሩትን ኢትዮጵያዊያን በልዩ የግብዣ ጥሪ በመጋበዝ ኤ ሲፒ ሀውስ acp house በተባለው የአፍሮ ካረቢያን ህንጻ አዳራሽ ሞቅ ደመቅ ያለ ድግስ ማድረጉን የግንቦት 7 ዜና ዘጋቢ ከብራስልስ ከተማ ከላከልን ዜና ለማወቅ ተችሎአል።

በዕለቱ በግብዣው ላይ ከተገኙት በርካታዎቹ የፈረደባቸው የትግራይ ክልል ተወላጆች እንደሆኑና በሁለተኛ ዜግነት በሚኖሩበት የስደት አለም ለፍተው ጥረው ያገኙትን ገንዘብ አገራቸው ውስጥ በማስገባት አንዳንድ አቅም የፈቀደላቸውን ሥራዎች ለመስራት የሚፈልጉ ከወያኔ ጋር ካልተሞዳሞዱ በቀር ይህ ህልማችው እውን የሚሆን የማይመስላቸው ስጋትና ፍርሃት የሚያርበደብዳቸው ዜጎች እንደሆኑ ለማወቅ መቻሉን ዘጋቢያችን ከላከልን ዜና ለመረዳት ተችሎአል።

በዕለቱ ግብዣ ላይ የተገኙ አንዲት ሴት ወይዘሮ ስለድግሱ የተሰማቸውን አስተያየት እንዲሰጡ በተጠየቁበት ወቅት፤ የኢትዮጵያን አድስ አመት እናክብር በማለት የአዲስ አመት መግቢያ ተከብሮ ባበቃ በወሩ በተደረገልን በዚህ ግብዣ የተለመደውን የልማትና የ ዕድገት ፕሮፖጋንዳቸውን ሊግቱን አስበው እንደጠሩን እያወቅን ነው የመጣነው ፤እንደጠረጠርነውም አንተ እራስህ በአዳራሹ ውስጥ ተገኝተህ የሰማሄው ሆኖአል በማለት ብርሃነ ገብረክርስቶስ ሰልመጪው የወያኔ 5 አመት የልማትና የእድገት ዕቅድ የደሰኮረበትን አጋጣሚ አስታውሰዋል።

ብርሃኔ ገብረክርስቶስ ለዲግሱ የተሰበሰቡትን አንኳን ደህና መጣችሁ በማለት የመክፈቻ ንግግር ካሰማ ቦኋላ የምንሊክን ቤተመንግሥት የተቆጣጠሩት አለቆቹ የኢትዮጵያን ህዝብ አይናችሁን ሸፍኑና ላሞኛችሁ የሚሉበትን ባዶ የልማትና የ እድገት ፕሮፖጋንዳውን ከደሰኮረ ቦኋላ ትግራዋይ ያልሆኑትን ሰራተኞች ከ ኤምባሲው ሙሉ በሙሉ በማባረር በምትካቸው የተተኩትን የህወሃት አባላት የሆኑ የትግራይ ተወላጅ የስርዓቱ ዲፕሎማቶችን አንድ በአንድ ወደ መድረኩ እየጠራ ለተጋባዦቹ አስተዋውቆአቸዋል ። የብርሃኔ ገብረክርስቶስ የ5 አመት የትራንስፎርመሽን ፕላን ንግግር ያስገረመው አንድ የግብዛው ተሳታፊ እነኚህ ሰዎች ሲዋሹ ትንሽም አይሸማቀቁም ሲል ተደምጦአል። ከ5 ኢትዮጵያዊ አንዱ የሚበላውን አጥቶ ለዕለት ጉርሱ አለም አቀፍ የምግብ እርዳታ ላይ በተንጠለጠለበት ወቅት ወያኔ ርካሽ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻውን ከባህር ማዶ ለማሻጋር በብዙ መቶ ሺ ዶላር የሚቆጠር የውጪ ምንዛሪ ከደሃው ጉሮሮ እየነጠቀ በምቾት የሚኖረውን ኢትዮጵያዊ ለመደለል ማባከኑ ይዋል ይደር እንጂ በታሪክና በህግ ፊት እንደየሚያስጠይቅ አይጠረጠርም ብለዋል አስተያየት ሰጪው።

ወያኔ በትግል ላይ በነበረበት ወቅት በ1977 የድርቅ አደጋ ለተጎዱት የትግራይ ረሃብተኞች ከአለም አቀፍ ለጋሾች ተሰጥቶ የነበረውን በመቶ ሚሊዮን ዶላር የሚቆጠር ገንዘብ የህወሃትን ወታደራዊ አቅም ለመገንባት እንደተጠቀመበት በወቅቱ ከፍተኛ የህወሃት አመራር አባላት የነበሩት ዶክተር አረጋዊ በርሄና አቶ ገብረመድህን አረአያ ማጋለጣቸውን ቢቢሲ የተባለው አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን በሰፊው እንደዘገበ ይታወቃል።