ይሄይስ ተኣምኖ በእግዚአብሔር (ይሄይስ አዕምሮ)
ይሄይስ አዕምሮ
እንደምን ሰነበታችሁልኝ! ባገራችን አንድ አባባል አለ፤ ”ከብቶች እንኳን በየፊናቸው ዱር ውለው ማታ ሲገናኙ ’እምቡዋ’ በመባባል ሠላምታ ይለዋወጣሉ” የሚል። በሌላም በኩል ”እንደከብት ዝም ብለህ አትቀላቀል” የሚለውን ቢፃዊ ግሳጼም ሳንዘነጋ። በ’ርግጥም ነገርን በሠላምታ መጀመር ጥሩ ነው – አሁንም ”ከሺህ ሠላምታ አንድ ሜታ!” ወይም ሦስት ጊዜ ሠላምታ አንዱ ለነገር ነው!” የሚባሉትን ፀረ-ሠላም(ታ) ኃይሎች ማለቴ አባባሎች ሳንረሳ። እናም ሠላምታየ በያላችሁበት ይድረሳችሁ።