የእስራኤልና ፍልስጤም መበቃቀል

የዘመነ-ዘመናቱ ፀሎት፤ ድርድር፤ የዲፕሎማሲ ጥረት ብዙዎች ብዙ ጊዜ እንዳሉት«ከልብ እና ፍትሐዊ» ሥላልሆነ—ሠላም የለም።ከልብ የሚደረገዉ ፖለቲካዊ መደባባት፤ ወታደራዊ መገዳደል፤እና መበቃቀል ግን ጥንትም-ድሮም ዘንድሮም አለ።