ከ12 ቢሊዮን ብር በላይ የተመደበለት የመንገድ ፕሮጀክቶች በታቀደላቸው ጊዜ አልተጠናቀቁም

(በታምሩ ጽጌ)

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን እ.ኤ.አ ከ2004 ጀምሮ እስከ 2010 ድረስ ግምቱ ከ12 ቢሊዮን ብር በላይ የሆነ የመንገድ ፕሮጀክቶች ለተለያዩ የውጭና አገር በቀል ተቋራጮች ቢሰጡም፣ በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ ሊጠናቀቁ አለመቻላቸውን ለሥራው ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡