በፑንትላንድ ከሞት የተረፈው ኢትዮጵያዊ እስካሁን አልተፈታም

– እህቱ በባህሉ መሠረት ለጋብቻ ተጠይቃለች

ከሶማሊያ ተገንጥላ ራሷን በምታስተዳድረው ፑንትላንድ ቦሳሶ ከተማ ውስጥ የሞት ፍርድ ተፈርዶበት በድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) የገንዘብ ልገሳ የተረፈው ኢትዮጵያዊው አስመሮም ኃይለ ሥላሴ፣ እስካሁን ድረስ አለመፈታቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡