ሰበር ዜና- ትዕዛዙ የማን ይሆን? – ከስለሺ ሐጎስ
የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ ያዘጋጀው የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡ በመሀል ፖሊሶች አስተባባሪውን እንፈልጋለን ብለው በሆቴሉ ሰዎች መልዕክት ላኩ ከነብዩ ሀይሉ ጋር ሪሴብሽን ሄጄ አገኘናቸው፡፡ እነሱም ፕሮግራሙን አቋርጣችሁ ንገራቸውና አሁኑኑ ተበተኑ የሚል ቀጭን ትእዛዝ አስተላለፉ፡፡ ለምን ብንል? መልሱ- ትእዛዝ ነው!! የሚል ሆነ ነብዩ ፈጠን ብሎ
“እሺ ለተሳታፊዎቹ እንንገራቸውና እንበተናለን”
ብሎ ወደ አዳራሹ ተመለስን፡፡
አሁን ፕሮግራሙ ቀጥሏል፡፡ ፖሊሶቹም ሪሴብሽን ናቸው፡፡ እኛም ለተሳታፊው ቃል ሳንተነፍስ ለፌስቡክ ተነፈስን፡፡
