ሰብዓዊ መብት በኢትዮጵያና የጀርመን ምክር ቤት
የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ እንደሚያሳስባቸው የጀርመን የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አባላት አስታወቁ። በምክር ቤቱ የሰብዓዊ መብት ኮሚቴ አባላት አሳሳቢ ካሏቸው ጉዳዮች ውስጥ በአዲሱ የኢትዮጵያ የፀረ አሸባሪነት ህግ ሽፋን በኢትዮጵያ የተለያየ አስተሳሰብ ባላቸው ጋዜጠኞችና በተቃዋሚ ቡድኖች ላይ የሚካሄደው ክትትል አንዱ ነው ። የበርሊኑ ዘጋቢያችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል በጀርመን የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የነፃ ዲሞክራቶቹ ፓርቲ ተወካይ ማርቲና ሺስተርን አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል። ያዳምጡ