የፋሽስቱ የወያኔ አገዛዝ ፖሊሲ ባስከተለው የኑሮ ደረጃ ግሽበት ተስፋ የቆረጡ ዘጎች አገራቸውን ጥለው በብዛት እየተሰደዱ መሆኑ ተገለጠ

ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ ወደ ስልጣን ከመጣበት ጊዜ አንስቶ ሃገራቸውን ለቀው ለስደት የሚዳረጉት ኢትዮጵያዊያን ቁጥር እጂግ እያሻቀበ መምጣቱና በታሪክ ታይቶ ከማይታወቅ ደረጃ ላይ መድረሱ ታወቀ።

ሃገሪቱን ለቀው ወደውጪ ሃገራት በሚሰደዱ ኢትዮጵያዊያን ዙሪያ ለሚጠናቀረው መረጃ ቅርብ የሆኑ የውስጥ ምንጮቻችን እንዳረጋገጡት በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያን በመልቀቅ ወደ የመንና ሱዳን የሚሰደዱት ኢትዮጵያዊያን ብዛት በእጅጉ አስደንጋጭ እየሆነ መጥቱአል።

ዘጋቢያችን የውስጥ ምንጮቹን በመጥቀስ በላከልን ዘገባ ላይ እንዳመለከተው፣ በተለይም ከአማራ ክልል ሃገራቸውንና ቀያቸውን ለቀው የሚሰደዱ ኢትዮጵያዊያን የከተማ ነዋረዎች ብቻ ሳይሆኑ ገበሬዎች ጭምር መሆናቸው ታውቁአል። መረጃዎቹ እንዳረጋገጡት በደቡብ ጎንደር በየሳምንቱ ከ250 እስከ 300፣ በሰሜን ወሎ ከ300 እስከ 450፣ በደቡብ ወሎ ከ200 እስከ 300፣ በጎጃም ከ400 እስከ 550 የሚደርሱ ገበሬዎችና የከተማ ነዋሪዎች ወደ የመን፣ ሱዳንና ሌሎች የጎረቤት አገሮች በገፍ እንደሚሰደዱ ለማወቅ ተቺሉአል።

በተለይም ከአማራው ክልል ሃገራቸውን ለቀው የሚሰደዱት ኢትዮጵያዊያን ቁጥር ያሻቀበበት ዋነኛ ምክንያት ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ በህዝብ ላይ እያደረሰ ያለው ማለቂያ የሌለው በደል፣ በየጊዜው የሚጨምረው የኑሮ ውድነት እና የእርሻ መሬት ጥበት መሆናቸው ታውቁአል።

ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ የስልጣን እድሜውን ለማራዘም ካለው እኩይ ፍላጎት የተነሳ የተወሰኑትን በሽብርተኝነት፣ ሌሎችን፣ በሃይማኖት እንዲሁም አብዛኛውን ህዝብ በጠመንጃ ሃይል በማስፈራራት ላይ መሆኑ በስፋት ሲዘገብ የቆየ ከመሆኑም በላይ የህዝብ ቁጥር መጨመር፣ የእርሻ ምነሬት እጦት እንዲሁም አለ የሚባለው ለም መሬት ለውጭ ባለሀብቶች እየተሰጠ መሆኑ ችግሩን እንዳባባሰው በርካቶች ይስማማሉ።