የጥሬ ወርቅ ግዥ ከብሔራዊ ባንክ ብቻ ሊሆን ነው

– ወርቅ ቤቶች አሁን እየሸጡ ያሉት ወርቅ ምንጩ አይታወቅም

በወርቅ ግብይት የተሰማሩ የጌጣጌጥ አምራቾችና ጌጣጌጥ ለማምረት ማረጋገጫ የተሰጣቸው ወርቅ ቤቶች፣ ለሚሠሯቸው ጌጣጌጦች ግብዓት የሚሆነውን ጥሬ ወርቅ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ብቻ ገዝተው እንዲጠቀሙ የሚያስገድድ መመርያ፣ ከመጪው ሳምንት ጀምሮ ተግባራዊ ሊደረግ ነው፡፡