የኢሰመጉ ስምንት ሚሊዮን ብር ዕግድ ፀና

የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማኅበራት ኤጀንሲ፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) ሕግ ከሚፈቅደው ውጪ የሰበሰበው ስምንት ሚሊዮን ብር ነው በሚል፣ ከባንክ እንዳይንቀሳቀስ የሰጠውን ውሳኔ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አሥራ አንደኛ ፍትሐ ብሔር ልደታ ምድብ ችሎት አፀና፡፡