የዕርዳታ ገንዘብ ለግል ጥቅም አውለዋል የተባሉ አፈ ጉባዔና ግብረ አበሮቻቸው ተከሰሱ

ለአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችና መሠረተ ልማት ሥራዎች ማካሄጃ ዩኒሴፍ በዕርዳታ የሰጠውን ገንዘብ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት አፈ ጉባዔና አምስት ግብር አበሮቻቸው ለግል ጥቅም አውለዋል በሚል ጥቅምት 22 ቀን 2004 ዓ.ም. ክስ ተመሠረተባቸው፡፡