‹‹ኤርትራ እንደ አንድ አገር የመቀጠል ዕድሏ እየጨለመ ነው›› ፕሮፌሰር ዮሴፍ ማግኔታ

የቀይ ባህር አፋር ዲሞክራሲያዊ ድርጅት የኤርትራ ቀይ ባህር አፋር ሕዝብን ‹‹ራስን በራስ የማስተዳደር እስከመገንጠል›› መብት ለማረጋገጥ በትጥቅ ትግል ላይ የተሰማራ ድርጅት ነው፡፡ ድርጅቱ ጥቅምት 13 ቀን 2004 ዓ.ም. የተጠናቀቀውን 3ኛ ሕዝባዊ ኮንፈረንስ በሰመራ (አፋር) አካሂዷል፡፡