በአምስተርዳም እንዳየነው፤ የተሳካ የስፖርት ፌስቲቫል፤ ያልተሳካ የባህል ትእይንት
ልጅ ተክሌ ከአምስተርዳም
ስፖርትና ፖለቲካ፦ ከቫንኩቨር እስከ አምስተርዳም
መቼም ሰዊትዘርላንድና ኮለን ተጫውተው ሰዊትዘርላንድ ዋንጫ በላ። በዝግጅቱም ላይ በአስር ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ተገኝተው ነበር። ከጣሊያን እስከ ኖርዌይ እስከ እንግሊዝ የመጡ ቡድኖች ተጫውተው … የሚል ጽሁፍ አትጠብቁም። ከዚያም ጠልቀን መሄድ አለብን። ፈርዶብኝ ይሄ ክፉኛ የተጸናወተኝ ሁሉንም ነገር በፖለቲካ መነጽር የማየት በሽታ ጸንቶብኛል።