በደቡብ ክልል ዓይነ ስውር ልጃቸው የታረደባቸው ወላጆች ‹‹የፍትሕ ያለህ›› እያሉ ነው

– ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ደብዳቤ ጽፈዋል

(በታምሩ ጽጌ)

በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት በወላይታ ዞን በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ የመርሙማ ቀበለ ገበሬ ማኅበር ነዋሪ የሆኑ ወላጆች፣ ዓይነ ስውር ልጃቸው በግፍ አገዳደል እንደበግ ታርዶና ሰውነቱ ተተልትሎ ሕይወቱ በማለፉ ‹‹የፍትሕ ያለህ›› በማለት ለጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ደብዳቤ ጻፉ፡፡