አክሱማዊነትን ያልተረዳው አክሱማዊ – (በእውቀቱ ስዩም) Ethiopia Zare October 31, 2011 Tagged with addis ababa, Ethiopia, health, import/export, politics አስተሳሰብህ የሰፈር አጨዋወትህ ለማፈር ሁኔታህ ሁሉ ባዳ ነው አንተን ማስቀመጥ ዕዳ ነው። ተመስገን ተካ 1990ዓ.ም ሰሞኑን የጌቶቻችንን የትጥቅ ትግል ታሪክ የሚዘግቡ መፃሕፍት ታትመው እየወጡ ነው፡፡ በአብዛኛው ተመሳሳይ ናቸው። የተዋጋነው ዴሞክራሲ ለማስፈን፣ ጭቆናን ለማስወገድ፣ ብሄረሰቦችን እኩያ ለማድረግ ስንል ነው የሚል ይዘት አላቸው። ማንም አንጋፋ ታጋይ፣ ያማረኝን ለመብላት፣ ጄት የሆነ መኪና ለመንዳት፣ የእሥር ቤት ቁልፍ በእጄ ለማስገባት ስል ነው የተዋጋሁት ብሎ እንዲተርክልን አንጠብቀውም።