ቴዲ አፍሮ በሞት ልትነጠቅ አንድ ቀን ለቀራት ነፍስ ደረሰ

ጥቅምት 8 ቀን 2004 ዓ.ም. ፑንትላንድ ውስጥ የሞት ፍርድ ውሳኔ ከተላለፈበት በኋላ፣ የተጠየቀውን የነፍስ ካሣ ክፍያ በአሥር ቀናት ውስጥ ማለትም ጥቅምት 17 ቀን 2004 ዓ.ም. ድረስ ካልፈጸመ፣ ውሳኔው ተግባራዊ እንደሚሆን የተነገረውን ግለሰብ፣ ግድያው ሊፈጸምበት አንድ ቀን ሲቀረው፣ ድምፃዊው ቴዎድሮስ ካሣሁን (ቴዲ አፍሮ) የተጠየቀውን የነፍስ ዋጋ 700 ሺሕ ብር ከፈለ፡፡