“ይህ – የታገልንለትን ጉዳይ አለማወቅ ነው”
ኮሎኔል መንግስቱ ኃ/ማርያም በአንድ ወቅት በፈፀሙት ድርጊት ተፀፅተው ይቅርታ ይጠይቁ እንደሁ በገነት ‹ማስታወሻ› ላይ ሲጠየቁ ‹‹ማንን ነው ይቅርታ የምጠይቀው? ወያኔን? ወያኔ እኔን ይቅርታ ጠይቆኛል?...ይህ የታገልንለትን ጉዳይ አለማወቅ ነው›› በማለት ጥያቄውን በጥያቄ መልሰዋል፡፡ መንግስቱ በአስተዳደራቸው ማክተሚያ ሰሞንም፣ በመንግስት መገናኛ ብዙሐን እንዲህ ብለው ነበር፡፡ ‹‹ለአገሬና ለወገኔ ይበጃል ብዬ ባደረግኩትና በተሳተፍኩባቸው ተግባሮች ሁሉ በግሌ ሕሊናዬን የሚወቅሰኝ ነገር የለም›› ብለዋል፡፡
‹‹መ››ንግስቱ እና ‹‹መ››ለስ
መንግስቱና መለስ እያደር የሚያመሳስላቸው ነገር ተበራክቷል፡፡ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ነጋሶ ጊዳዳ ‹‹የነጋሶ መንገድ›› በተሰኘው ግለታሪካቸው እንደነገሩን የሕወሓት ተገንጣይ ቡድን ተሸንፎ ሲወጣ የነመለስ ቡድን (በተለይ አቶ መለስ) ‹‹ጃኬታቸውን አስወልቀን ሸኘናቸው›› እያሉ ሲፎክሩ ነጋሶ መለስን ‹‹መንግስቱን፣ መንግስቱን መሰልከኝ›› ብለዋቸዋል፡፡ እውነት ነው፤ (መ)ንግስቱና (መ)ለስ (መ)ንትያ ናቸው፡፡ እስኪ በዝርዝር እንመልከተው…
- አነጋገር - መለስ ንግግር አዋቂ ናቸው፡፡ መንግስቱም ንግግር አዋቂ ነበሩ፡፡ መንግስቱ ለቃላት አመራረጥ አይጨነቁም ነበር፡፡ ስድብና ድንፋታ በየአደባባዩ አያሳፍራቸውም ነበር፡፡ መንግስቱ ከወረዱ ከ20 ዓመት በኋላ እርሳቸውን ከስልጣን ያስወገዱት አማፂያን መሪም ይኸው የሳቸውን ፈር እየተከተሉ ነው፡፡ መለስ በየፓርላማው አባሎቻቸውን በሚያስቀው ስድባቸው አንጀታቸው ስለማይርስ - አሁን፣ አሁን የእጅ እንቅስቃሴያቸው እና የትከሻቸው መናጥ የስድብ አምሮታቸውን ያሳብቅባቸዋል፡፡
- ነፍስ ማጥፋት - የመንግስቱ ኃ/ማሪያም ኢሠፓ ከተቃዋሚዎቹ ኢሕአፓ ጋር በከተማ መሃል ሽምቅ ውጊያ የጀመረው ገና በስልጣኑ አፍላ ዘመን ነው፡፡ ቀይሽብር እና ነጭሽብርን በየበኩላቸው አውጀው ሲገዳደሉ ስለወደፊቷ ኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ አላሰቡም ነበር፡፡ (ለመንግስቱ አምባገነንነት የኢሕአፓ ድርሻ ቀላል አይደለም) የአቶ መለስ ደግሞ ይብሳል፡፡ ደርግ አውጆ ሲገድል፣ ኢሕአዴግ ከቻለ በድብቅ/በሰበብ ካልቻለ ደግሞ ፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም በአንድ ጽሁፋቸው ላይ እንዳሉት ‹‹don’t kill them, break them›› የተሰኘ ዘዴ ይከተላል፡፡ የመለስ ዜናዊ ሰራዊት የጥይት አሩሩን ያሳረፈው እንደኢሕአፓ የመሳሪያ ትግል በጀመሩ ተቃዋሚዎች ላይ አይደለም፡፡ ከድንጋይ መወርወር በላይ አቅም በሌላቸው ወጣቶች ላይ ነው፡፡
- ስልጣን - መንግስቱ ለ17 ዓመታት ያህል መተኪያ ያልተገኘላቸው መራሄ መንግስት ሆነው ነበር፤ አሁን ደግሞ መለስ 25ኛቸውን ዓልመው እየተጓዙ ነው፡፡
- ነፃነት - በደርግ ጊዜ መንግስትን መቃወም ቀርቶ ለመቃወም ማሰብም የሚያስፈራ ነገር ነበር፡፡ አሁንም ነገሩ ብዙ የተለየ አይደለም፡፡ ሁሉም ሰው መቃወም ይፈራል፤ በቀጥታም ባይሆን በተዘዋዋሪ ዋጋውን እንደሚቀምስ ያውቀዋል፡፡ የእንግሊዙ Legatum Institute አምና ባወጣው የProsperity Index ላይ ኢትዮጵያ በግለሰብ ነፃነት ከ110 አገሮች 93ኛ እና በሕዝቦቿ የደህንነት ስሜት ደግሞ 103ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠች የፈሪዎች አገር ሁናለች - የነፃነቱ ብዛት፡፡
- ኢኮኖሚ - በደርግ ዘመን (ዕድሜ ለአማፅያን) መንግስቱ አብዛኛውን የበጀት ፈሰሳቸውን ለጦርነት በማዋላቸው የኢትዮጵያ ሕዝብ በረሃብና ችግር አለንጋ እየተገረፈ ነበር፡፡ አሁንም በመለስ ሕንፃዎች በሚፈሉበት፣ መንገዶች እየዘመኑ ባሉበት ዘመን ድህነት ከነኩራቱ ለ‹‹99 በመቶዎቹ›› ሕዝቦች ይታያቸዋል፡፡ ከላይ የጠቀስኩት ኢንዴክስም ይህንኑ ያረጋግጣል፤ ከ110ሩ ሃገራት 106ኛ ላይ የመለስ ኢትዮጵያ ትገኛለች፡፡
ስለዚህ መለስ ከመንግስቱ ይለያሉ ወይስ አይለዩም?
ማወዳደርን ምን አመጣው?
መለስ ራሳቸው አሁን፣ አሁን አስተዳደራቸውን ከመንግስቱ ዘመን አስተዳደር አንፃር መመዘን ጀምረዋል፡፡ ምነው እንኳን ባለፈው ኦስሎ ውስጥ ለገጠማቸው ተቃውሞ የሰጡት ማስተባበያ ‹‹በመንግስቱ ዘመን ሰዎች ሲገደሉ ለተገደሉበት ጥይት ሒሳብ ይከፍሉ ነበር›› አላሉም? ነገሩን የታዘቡት የአዲስ ነገር ጋዜጠኞች ‹የአገር ቤት ጋዜጦች› በተሰኘው ሳምንታዊ ክለሳቸው ‹‹መለስ ይህን ያሉት፣ አሁን እኛ ነን የጥይቱን ዋጋ የምንሸፍነው ለማለት ፈልገው ይሆን?›› ሲሉ ተሳልቀዋል፡፡
መለስ ማነፃፀር ከጀመሩ አይቀር እኔም አንድ ነገር ልጨምርላቸው፡፡ መንግስቱ ኃይለማርያም ሲታገሉ የነበረው ለምን እንደሆነ ማስታወስ ነበረባቸው፡፡ መንግስቱ ኃ/ማርያም ሲታገሉ የነበሩት፤ ለኢትዮጵያ አንድነት፣ ለኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ነበር፡፡ ከመለስ ሰራዊት ጋር ሲታገሉ በመክረማቸው ነበር አምባገነን አድርጎ ያስቀራቸው፡፡ (በርግጥ የርሳቸው፣ የፍላጎት ድርሻ ውስጡ ቢኖርም) የመንግስቱ አስተዳደር ከጊዜያዊ ወታደራዊ መንግስትነቱ ለመላቀቅ እንኳን ፋታ ሳያገኝ ነው በትግል ወጥቶ በትግል የኮበለለው፡፡ መንግስቱ የፈሩት አልቀረም፤ የኢትዮጵያ አንድነት በብሔር ዘመም አስተሳሰቦች ከተናጋ ውሎ አድሯል፣ የባሕር በር ባለቤትነታችንም ድሮ ቀረ፡፡
ምናልባት የመንግስቱን የጭካኔ ዘመን ስላልደረስኩበት ሊሆን ይችላል፤ ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን ለኔ ‹‹ለሰላም ሲባል›› የአገራቸውን ድንበር በሱዳንም፣ በሶማሌያም፣ በኬንያም፣ በኤርትራም በኩል እየቆረሱ ያልሰጡት፣ (መንገዱን ባያውቁበትም) ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያዊነት ያላቸው ፍቅር የማያጠያይቀው፣ ሚሊዬነር ሊሆኑ ቀርቶ ለራሳቸው ምንም ቅሪት ሳያጠራቅሙ የኖሩት መንግስቱ፣ ይህንን ሁሉ መሆን ካልቻሉትና ከእርሳቸው (ኮ/ል መንግስቱ) ስህተት መማር ካልቻሉት ከአቶ መለስ ይሻሉኛል፡፡
አሁን ደግሞ፤ ኮሎኔል መንግስቱ ‹ትግላችን› በሚል በፀሃይ አሳታሚ (ከአሜሪካ) አማካኝነት እያሳተሙት ባለው የመጀመሪያው ቅጽ መጽሃፋቸው ላይ ‹‹የፖለቲካ ድርጅቶችም ሆኑ መሪ ግለሰቦች የሚመጡና የሚሄዱ አላፊዎች ሲሆኑ ሃገርና ሕዝብ ግን ዘላለማዊ ናቸው፡፡ ይህም ቢሆን በአንድ ታሪካዊ ወቅት መንግስታት፣ የፖለቲካ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች ያከናወኗቸው ገንቢም ሆነ አፍራሽ ተግባሮች ማንም ወደደ ጠላ የዚያ ሃገርና ሕዝብ ታሪክ ናቸው›› ብለዋል፡፡

I think this is like a joke! One smart generation is lost during the Mengistu era. As the ideology of the Dergue era was based on Marxist-Leninist theory that denies the existence of God, cruelty or inhumanity was the first discipline of the Dergue cadres. It is very difficult to write and documented each killing before and during “red-terror” monitored by the Dergue slauthers or cadres. I want to mention one thing that happened during that time at my school. I was 14 years old learning at grade nine, as usually I do, I went to my school early the morning, in the main entrance of the school, a man was shot on his back head by the Dergue cadres and was lying on his back, and a piece of paper was written on his back. I was very terrified and trying to return home but the cadres forced me to cross the dead and entered the school. The paper on his back was read as “red-terror”, reason, caught to deliver sugar for EPRP in Assimba. This is one of the many cruelty and inhuman atrocities done by the government of Butcher Mengistu. In reality, at this time it was awesome if the dictator apologizes to the victims, in my opinion the cruelty and inhuman action of Mengistu must be his personal history but not the innocent people of Ethiopia. In my opinion, dictator Mengistu plays a great role in the sovereign and territorial integrity of Ethiopia to fall under its enemies, Why? When the anti Ethiopia elements such as Shaebia and Weyane get success in military ground in unison, prominent Ethiopians such as professor Mesfin and others were asking Mengistu to make reconciliation(yeqr-leEgziabher) and to form a temporary peoples government(Yeadera-Mengist) but after a time he changes his mind and refuse the proposal and decided to cling into power to the last minute he flees to Zimbabwe, left the country to its enemies. So, how can we say that Mengistu likes his country?, because of his ignorant and power monger, Mengistu and his associates are responsible for all Weyane”s hidden agenda made on the country’s sovereignty and territorial integrity. A lot is expected from the present and next generation to heal the country’s sovereignty and territorial issues. It is our responsibility to teach the current generation his countries and his ancestors real history as well as how the current government is destructing the country. “God Bless Ethiopia.”
የምታቀር ታማኝነቱ ምን ያህል እውነት ከሆነ በጣም ይገርማል የኢትዮጵያ ጉድ ምን ይሻላል ትላላቹ ጎበዝ መጠረሻውስ እንዲት ነው
እውነት ነው ግን የሚገርመኝ እግዛብሔር አምላክ ከላይ ከሠማይ ሆኖ ሲያይ ምን ይል ይሆን የኢትዮጵያ ነገር መቼ ነው የሚፈጥነው እስከመቼ በችግር በጎስቁልና በርሀብ ትቀጣለች የኢትዮጵያዊ ሁሉ ወደ እ/ር ፊቱን ይመልስ መልክቴን አስተላልፎልኝ እባካችሁ፡፡