የቀድሞው የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ምደባ አልተሰጣቸውም

•    በአዲስ አበባ ሹም ሽር ስለመደረጉ ማስተባበያ ተሰጥቶ ነበር

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጥቅምት 12 ቀን 2004 ዓ.ም. ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው ከኃላፊነት ያነሳቸው ምክትል ከንቲባው አቶ ከፍያለው አዘዘ፣ በአስተዳደሩ ውስጥ ባሉ በማናቸውም ኃላፊነቶች ወይም የሥራ መደቦች እንዳልተመደቡ ታወቀ፡፡