አወዛጋቢው የአዲስ አበባና የኦሮምያ ልዩ ዞን ማስተር ፕላን

ማስተር ፕላን የኦሮምያ ክልልን ጥቅም ያስቀራል የአካባቢውን ገበሪ ያፈናቅላል የሚሉና የመሳሰሉ ተቃውሞዎች እየተሰነዘሩበት ነው ። መንግሥት ግን ማስተር ፕላኑ የተዘጋጀው በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ የኦሮምያ ልዩ ዞን ከተሞችም ከአዲስ አበባ ጋር አብረው እንዲያድጉ ታስቦ ነው ይላል ።