በ53 ሚሊዮን ዶላር የእናቶችንና የሕፃናትን ሞት ለመቀነስ ፕሮግራም ተቀረፀ
• 6.8 ሚሊዮን ዜጎች የፕሮግራሙ ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሏል
የአሜሪካ ሕፃናት አድን ድርጅት፣ ኢንጅን (ENGINE) በተባለው አዲስ የ53 ሚሊዮን ዶላር ፕሮግራሙ በአምስት ዓመታት ውስጥ የእናቶችንና ሕፃናትን አመጋገብ በማሻሻል ሞትን እንደሚቀንስ፣ በትናንትናው ዕለት በሸራተን አዲስ ባካሄደው የፕሮግራሙ መክፈቻ ዝግጅት ላይ አስታወቀ፡፡