አዋልዱ ለወለላዬ /የወለላዬ ልጆች/

በዓለማየሁ ታዬ [email protected] 

ረቡዕ አራተኛ ቀን ነው። እግዚአብሔር ባራተኛው ቀን የመዓልትና የሌት ብርሃናትን በየጽንፋቸው እንዲሰለጥኑ አዘዛቸው እነሱም ታዘዙት። በዚሁ አካሄድ ገጣሚው በሳምንቱ አራተኛ ቀን ትዝብቱን ቁጣውን ትግርምቱን ደስታውንና ሃዘኑን የሚያንጸባርቁ ሃሳቦችን በፈደል ዘር በግጥም ዘዬ እንዲሰለጥኑ አዘዛቸው እነሱም ታዘዙት።