ከአውሬ ተረፈ የተባለው የአዛውንቱ አፅም ውዝግብ አስነሳ

– ልጆቻቸው አፅሙ የሰው ሳይሆን የእንስሳ ነው ይላሉ

(በምዕራፍ ብርሃኔ)

ነዋሪነታቸው በሐረር ከተማ ንዑስ ቀበሌ 18 የቤት ቁጥር 455 የሆኑት የ70 ዓመቱ አዛውንት ሻምበል እሸቴ መንግሥቴ፣ በአውሬ ተበልቶ የተረፈ ነው ተብሎ በንድ የፖሊስ ባልደረባ አማካኝነት ሟች ለተባሉት ቤተሰብ የተሰጠው አፅም፣ በሐረሪ ፖሊስ መምሪያና  በሻምበል እሸቴ ቤተሰብ መካከል ውዝግብ ፈጠረ፡፡