የወያኔ አዲሱ ካቢኔ ተሿሚዎች
(ሪፖርተር) — በትናንትናው ዕለት በመለስ ዜናዊ አቅራቢነት የአዲሱ ካቢኔ ዕጩዎች ሹመት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲፀድቅ፣ ዘጠኝ የቀድሞ ሚኒስትሮች በአዲሱ ካቢኔ አልተካተቱም፡፡ የቀድሞው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ አዲሱ ለገሠ በቅርቡ መሰናበታቸው በኢሕአዴግ 8ኛው ጉባዔ ላይ በመገለጹ፣ በመንግሥት ሥራ እንደማይቀጥሉ ታውቋል፡፡ የቀድሞው የአቅም ግንባታ ሚኒስትር አቶ ተፈራ ዋልዋ በብአዴን ድርጅታዊ ጉባዔ ላይ ‹‹በቃኝ›› በማለታቸው እሳቸውም በአዲሱ ካቢኔ ውስጥ የሉበትም፡፡ የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ሥዩም መስፍንም እንዲሁ በአዲሱ ካቢኔ ውስጥ ምደባ አልታዩም፡፡
የቀድሞ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ ግርማ ብሩ፣ የሥራና ከተማ ልማት ሚኒስትር ዶ/ር ካሱ ኢላላ፣ የውኃ ሀብት ልማት ሚኒስትር አቶ አስፋው ዴንጋሞ፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር መሐመድ ድሪር፣ የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ሐሰን አብደላና የሴቶች ጉዳይ ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፊያት ካሚል በአዲሱ ካቢኔ ውስጥ የሉበትም፡፡
አቶ አዲሱ ለገሠ፣ አቶ ተፈራ ዋልዋ፣ አቶ ሥዩም መስፍንና አቶ ግርማ ብሩ ቀደም ሲል በአዲሱ ካቢኔ ውስጥ እንደማይካተቱ ሲነገር የነበረ ቢሆንም፣ የተቀሩት ሚኒስትሮች የቀድሞ መሥርያ ቤቶቻቸው በአዲስ አወቃቀር ሲደራጁ በሌሎች አዳዲስ ሚኒስትሮች ተተክተዋል፡፡
የአዲሱ ካቢኔ ሹማምንት ዝርዝር እንደሚከተለው ነው፡-
| የተሾሙበት ኃላፊነት | የተሿሚዎች ስም ዝርዝር |
| ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር | አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ፣ የኢሕአዴግ ም/ሊቀመንበር፣ (ደኢሕዴን) |
| የአገር መከላከያ ሚኒስትር | አቶ ሲራጅ ፈጌሳ (ደኢሕዴን) |
| የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር | ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም (ደኢሕዴን) |
| የፍትሕ ሚኒስትር | አቶ ብርሃን ኃይሉ (ብአዴን) |
| የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር | አቶ ጁነዲን ሳዶ (ኦሕዴድ) |
| የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር | አቶ ሱፊያን አህመድ (ኦሕዴድ) |
| የግብርና ሚኒስትር | አቶ ተፈራ ደርበው (ብአዴን) |
| የኢንዲስትሪ ሚኒስትር | አቶ መኮንን ማን ያዘዋል (ብቸኛው የፓርቲ አባል ያልሆኑ ባለሥልጣን) |
| የንግድ ሚኒስትር | አቶ አብዱራህማን ሼክ መሐመድ (ሶሕዴፓ) |
| የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር | አቶ ደሴ ዳርጌ (ደኢሕዴን) |
| የትራንስፖርት ሚኒስትር | አቶ ድሪባ ኩማ (ኦሕዴድ) |
| የመገናኛና ኢንፎርሚሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር | አቶ ደብረ ጽዮን ገ/ሚካኤል (ሕወሓት) |
| የከተማ ልማትና ግንባታ ሚኒስትር | አቶ መኩሪያ ኃይሌ (ደኢሕዴን) |
| የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር | አቶ አለማየሁ ተገኑ (ኦሕዴድ) |
| የማዕድን ሚኒስትር | ወ/ሮ ስንቅነሽ እጅጉ (ኦሕዴድ) |
| የትምህርት ሚኒስትር | አቶ ደመቀ መኮንን (ብአዴን) |
| የጤና ጥበቃ ሚኒስትር | ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም (ሕወሓት) |
| የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር | አቶ አብዱልፈታህ ሐሰን (ሶሕዴፓ) |
| የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር | አቶ ዓሚን አብዱል ቃድር (አፋር) |
| የሴቶች፣ ወጣቶችና ሕፃናት ሚኒስትር | ወ/ሮ ዘነቡ ታደሰ (ብአዴን) |
| የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ (በሚኒስትር ማዕረግ) | አቶ በረከት ስምዖን (ብአዴን) |
| በተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ተጠሪ (በሚኒስትር ማዕረግ) | ወ/ሮ አስቴር ማሞ (ኦሕዴድ) |
| የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዳይሬክተር (በሚኒስትር ማዕረግ) | አቶ መላኩ ፈንታ (ብአዴን) |