አቡጊዳ – አቶ አንዱዋለምና አቶ እስክንድር በባለቤቶቻቸዉ ተጎበኙ
ሐሙስ ጥቅምት ሁለት ቀን 2004 ዓ.ም ፣ ከሰዓት በኋላ በስምንት ሰዓት አካባቢ እንደሚቀመጥ ቀጠሮ የተያዘለት፣ እነ አቶ አንዱዋእም አርጌና እስክንድር ነጋ ጨምሮ በሽብር ሥራ የተከሰሱ ኢትዮጵያዉያን ጉዳይ የያዘዉ ችሎት፣ በድንገት ተከሳሾች አስቀድሞ ሳይነገራቸዉ፣ የዚያን ቀን በጠዋቱ ሁለት ሰዓት መቀመጡን ከአዲስ አበባ የደረሰ ዘገባ ያመለክታል።
ፖሊስ መረጃዎች ለማሰባሰብ ተጨማሪ ጊዜ ያሰፈልገኛል በማለቱ፣ ፍርድ ቤቱ ያለ ምንም ማመንታት ለፖሊሲ አስፈላጊዉን ጊዜ መስጠቱ ይታወቃል። በዚሁ ቀን ፖሊሲ መረጃዎቹን አቅርቦ የፍርድ ሂደቱ ይቀጥላል ተብሎ ቢጠበቀም፣ እንደገና ተጨማሪ ጊዜ ያስፈልገኛል ብሉ ፖሊስ የጠየቀ ሲሆን፣ የገዢዉ ፓርቲ አካል እንደሆነ የሚነገርለት ፍርድ ቤት ፣ አሁንም ያለ ምንም ማመንታት፣ የፖሊስን ጥያቄ ተቀብሎ፣ ተጨማሪ 28 ቀናት ለፖሊስ በመስጠት፣ በሰላም የሚታገሉ ዜጎች በእሥር እንዲቆዩ ወስኗል።
በተያያዘ ዜና፣ የአቶ አንዱዋለም አርጌ ባለቤት የሆኑት ዶር ሰላም፣ ዓርብ ቀን ጥቅምት አምስት ቀን፣ አቶ አንዱዋለምን በእሥር ቤት አግኝተዉ ያነጋገሩ ሲሆን ፣ በአቶ አንዱዋለም አካል ክሳት ከመታየቱ በስተቀር በጥሩ ሁኔታ እንደሚገኙ፣ በመፈሱን የጸኙ እንደሆነ ዶር ሰላም ገልጸዋል።
የአቶ እስክንድር ባለቤት ሰርካለም ፋሲልም በተመሳሳይ ሁኔታ ባላቤቷን የጎበኘች ሲሆን፣ አቶ እስክንድር ነጋም እንደ አቶ አንዱዋለም ከፍተኛ የመንፈስ ጽናት ጥንካሬ እንደሚታይበት፣ ለአላማዉ የቆረጠ እንደሆነም፣ ወ/ሮ ሰርካለም እንደገለጸች ዘጋቢዎቻችን ገልጸዉልናል።