በአዲስ አበባ የኢሕአዴግ ግምገማ ከፍተኛ ሹማምንት ከኃላፊነት ተነሱ

• አቶ ከፍያለው አዘዘ በአቶ አባተ ስጦታው እንዲተኩ ተወሰነ

የአዲስ አበባ ኢሕአዴግ አመራር ቡድን ጥቅምት 2 እና 3 ቀን 2004 ዓ.ም. ባደረገው ግምገማ፣ የከተማውን ምክትል ከንቲባ፣ የአዲስ አበባ ኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት ኃላፊና ሌላ የአዲስ አበባ የመዋቅር አባላትና ሥልጠና ዘርፍ ኃላፊን ከኃላፊነት ማንሳቱን ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡