የኢትዮጵያ ህዝብ፤ ከዚኽ ወዴት? (ክፍል 7 – አያልሰው ደሴ)

የኢትዮጵያ ህዝብ፣ አገር-ወዳድና ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች እና ኢህአዴግ፤ ከዚኽ ወዴት? ክፍል ሰባት

አያልሰው ደሴ (የግል አስተያየት)

… ኢዴኃቅ አዲሱ የኢህአዴግ መሪዎች በሀገራችን ላይ የተከተሉትንና ሥራዬ ብለው የተያያዙትን የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ ቅኝቶች አደገኝነት ጠንቅቆ የተረዳ በመሆኑ እነኛ አደገኛ ውጥኖች በተግባር እንዳይተረጎሙ ከጥንስሱ ጀምሮ በተቻለው መንገድ ሁሉ አምርሮ ታግሏል። ሆኖም በተጠቀሱት ዋና ዋና ምክንያቶች እነኝህን አደጋዎች ማስቀረት ቀርቶ ማዘግየት አልተቻለውም።