በኖርዎይ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን የፋሽስቱን መለስ ዜናዊ ጉብኝት በመቃወም የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

በእንግሊዝኛ አጠራሩ “Energy for All” ማለትም ሃይል ለሁሉም በሚል መርህ በኖርዎይ ሃገር ኦስሎ ከተማ ላይ በተካሄደ ባለው ዓለም አቀፍ ስብሰባ ንግግር ለማድረግ የተጋበዘው ዘረኛውና አምባገነኑ የወያኔ አገዛዝ ቁንጮ መለስ ዜናዊ፤ በኖርዎይና አካባቢዋ ከሚገኙ አጎራባች ሃገራት የተሰባሰቡ ኢትዮጵያዊያን ባደረጉት ከፍተኛ የሆነ የተቃውሞ ሰልፍ ምክንያት ተሸማቆና አንገቱን ደፍቶ ወደስብሰባ አዳራሽ እንዲገባና እንዲወጣ መገደዱን ዘጋቢያችን ከኖርዎይ ኦስሎ ከተማ ባስተላለፈልን ዘገባ ገለጸ።

በትናንትናው እለት በተካሄደው በዚሁ ስብሰባ እንዲገኝ የተጋበዘውን ዘረኛና አምባገነን ቁንጮ መለስ ዜናዊ ለመቃወም ብዛት ያላቸው ኢትዮጵያዊያን የተገኙ መሆኑ የታወቀ ሲሆን፣ በኦስሎ ከተማ በእለቱ የነበረውን ከፍተኛ ቅዝቃዜ በመቋቋም የተቃውሞ ሰልፉን ያካሄዱት ኢትዪኦጵያዊያን እልህና ቁጣ በተሞላበት መንፈስ በርካታ መፈክሮችን እያስተጋቡና የተቃውሞ ድምጻቸውንም ሲያሰሙ መዋላቸውን ዘጋቢያችን ከላከልን ሪፖርት ለማወቅ ተቺሏል።

እንደዘጋቢያችን ሪፖርት ተቃውሞውን ለማሰማት የተሰባሰበው ህዝብ የፋሽስቱ መለስ ዜናዊን ወደስብሰባ አዳራሽ ማምራት በርቀት በተመለከተ ጊዜ ቁጣው ፈንቅሎት ለሰልፍ የተፈቀደለትን ቦታ ጢሶ አንገቱን ለማነቅ በሆይታ በመነጎዱ ሥነሥር ዓት ለማስከበር በቦታው ከነበሩት የኖርዌዬ ፖሊሶች ጋር መጋጨቱን በዚህም የተነሳ ሶስት ኢትዮጵያዊያንን ለተወሰኑ ሰአታት ታስረው መለቀቃቸው ታውቆአል።

መለስ ዜናዊ በህዝባችንና በአገራችን ላይ የሚፈጽመውን ሰቆቃና ወንጀል ለማውገዝ የወጣው ሰልፈኛ ካሰማቸው መፈክሮች መካከል መለስ ዜናዊ ሽብርተኛ ነው መለስ ዜናዊ ዘረኛ ነው፣ መለስ ዜናዊ ነፍሴ ገዳይ ነው፣ መለስን ወደ ኖርዎይ ሳይሆን ወደ ሄግ ለፍርድ ላኩት፣ ዘረኛው መለስ ለፍርድ ከቀረበልን ወደሃገራችን ለመመለስ ዝግጁ ነን፣ ኖርዎይ መለስ ዜናዊን መጋበዟና ማስተናገዷ ውርደት ነው፣ በሽብርተኝነት ስም በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው የጅምላ እስራት ይቁም፣ ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ አሁኑኑ ይፈቱ፣ መለስ ዜናዊ አሁኑኑ ይወገድ፣ መለስ ዜናዊና አገዛዙ አሸባሪዎች ናቸው፣ የኖርዎይ መንግስት ለኢትዮጵያው አሸባሪ አገዛዝ የሚያደርገውን እገዛና ድጋፍ ያቁም የሚሉና ሌሎች መፈክሮች ይገኙበታል።

በኦስሎ ከተማ በተካሄደው በዚሁ ሰልፍ ኢትዮጵያዊያኑ የፖለቲካ የትግል መስመርና ዘር ሳይለያቸው በአንድነት ተቃውሞአቸውን ሲያሰሙ እንደነበር የገለጸው ዘጋቢያችን፣ በእለቱ የተቃውሞ ሰልፍ የኦሮሞ ነጻነት ግምባር፣ የኦጋዴን ነጻነት ግምባር፣ እንዲሁም የተለያዩ የተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጂቶች አባላት በጋራ ሆነው ተቃዉሞአችውን ሲያሰሙ ውለዋል።