ከዕለቱ ምርጥ አሣዛኝ ዜናዎች ጥቂቶቹ (ነፃነት ዘገዬ)

ነፃነት ዘገዬ

ዓለም በአሣዛኝ ዜናዎች መጥለቅለቅ ከጀመረች ዋል አደር ብላለች። አሁን አሁን የዜና ማሠራጫዎች ራሳቸው ክፉ ዜና ማወጅን በጣም ከመልመዳቸው የተነሣ መልካም ዜናን እንደቅንጦት እያዩት ይመስላል ብዙም ሲማረኩበት አይታዩም። እርግጥ ነው ከወደ አሜሪካን ሀገር በሣተላይት የሚሠራጭ ሱፕሪም ማስተር የሚባል ቴሌቪዥን አውቃለሁ።