እነ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ

እስረኞቹ ከ1ወር በኋላ ቤተሰቦቻቸውን ለመጀመሪያ ጊዜ አይተዋል

Ethiopia Zare (ሐሙስ ጥቅምት 2 ቀን 2004 ዓ.ም. October 13፣ 2011)፦ በማእከላዊ ፖሊስ ምርመራ የ28 ቀን የጊዜ ቀጠሮ የተወሰደባቸውና በሽብርተኝነት ክስ የተመሰረተባቸው እስክንድር ነጋ፣ አቶ አንዷለም አራጌና ሌሎች እስረኞች በድጋሚ ጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸው ወደማእከላዊ እስር ቤት ተመልሰዋል።