ማስታወቂያ፦ ንስረ ቃል የተሰኘ በአማርኛ ቋንቋ የመጽሐፍ ቅዱስን ጥቅስ መፊለጊያ ሶፍትዌር


ከዚህ በታች ያለውን ማስታወቂያ በኢ-ሜይል ያደረሱን አንድ ደጀ ሰላማዊ ናቸው። ጉዳዩ ለሁላችንም ጠቃሚ መሆኑን ስለምናምን እንደሚከተለው አቅርበነዋል።

++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++

  • ማንኛውም ሰው በነጻ ሊጠቀምበት ይችላል
 (http://www.meliyu.com):- በዓለማችን ላይ በጣም ተነባቢ ከሆኑት መጻሕፍት ውስጥ አንዱ መጽሐፍ ቅዱስ መሆኑ ይታወቃል:: ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ ከያዛቻው የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻህፍት ቍጥር አኳያ ከያንዳንዱ መጻህፍት ውስጥ ጥቅሶችንና  ሀረጐችን ነጥሎ መፊለጉ ለአብዛኛው ምዕመናንና የመጽሐፍ ቅዱስ ተጠቃሚዎች( ተማሪዎች) ፈታኝ ነበር:: ነገር ግን የዘመኑን የኮምፒውተር ፕሮግራሚንግ ቴክኖሎጂ በመጠቀም በአማርኛ ቋንቋ የመጽሐፍ ቅዱስን ጥቅስ መፊለጊያ ሶፍትዌር በቅርቡ ይፋ ሆኗል::
ንስረ ቃል የተስኘው ይህ ሶፍትዌር ማንኛውንም የመጽሐፍ ቅዱስ  ቃላትን  ከሁሉም የመጽሐፍ ቅዱስ  ክፍላት ውስጥ በሰከንዶች የሚፊልግ ሶፍትዌር ነው።
ይህ ሶፍትዌር ፍለጋውን የሚያካሂደውና ውጤቱንም የሚያሳውቀው በአማርኛ ቋንቋ መሆኑ ደግሞ ለአትዬጵያውያን መልካም የምስራች ነው።
ንስረ ቃል ፊልጐ ያገኛቸውን ጥቅሶችንና ሀረጋትን በተለያየ የሰነድ ቅርፀት( pdf,  html ) ማኖር የሚያስችል አቅም ያለው ሶፍትዌር ሲሆን ማንኛውም ሰው በነጻ ሊጠቀምበት ይችላል።
ይሄው ድረ ገጽ ብራና የተባለ የኢትዬጵያ ቋንቋዎች ቃላት ማቀናበርያ(word processor) ልዩ ሶፍትዌር በተጨማሪ ይፋ አድርጐአል።
ብራና ሶፍትዌር የአማርኛ ፤ የኦሮምኛ ፤ የትግርኛና የእንግሊዘኛ በይነ ገጾች( interface) አሉት።ብራና ሶፍትዌር የአማርኛ ፤ የኦሮምኛ ፤ የትግርኛና የእንግሊዘኛ ቃላት ማረሚያዎችን(spell check ) ያካተተ ነው።
ንስረቃልና ብራና የተስኙት ሁለቱ ሶፍትዌሮች  (http://www.meliyu.com/) በተባለው ድረ ገጽ በቀላሉ መመልከት ማግኘት ይቻላል።